December 29, 2013
ከዓለማየሁ መሀመድ (ክፍል 3)
አቧራው ጬሷል። ግለቱ ጨምሯል። ሙቀቱ አይሏል። የሳይበሩ ጦርነት ተጋግሏል። በሁሉም ወገኖች ትርፍና ኪሳራው ገና አልተሰላም። ከመነሻው ትርፋማ መሆኑ የተረጋገጠለት ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ዘና ፡ ከወንበሩ ለጠጥ ብሎ በትዝብት ፈገግታ ሁለቱን ወገኖች ይመለከታል። ቢቻለው ካራ አቀብሎ የፌስ ቡኩ ጦርነት ደም ወደ ሚያፋስስ ዕልቂት ቢቀየርለት ምንኛ በመረጠ?!

በእርግጥ እያሰበበት ነው። የመረጃ ምንጮቼ ሹክ እንዳሉኝ ከሆነ የህወሀት ስሌት እስከ እልቂቱ የሚሻገር ነው። ሰሞንኛዋ ግርግርም አራት ኪሎ ቤተመንግስ ተቀምራ፡ ዋሽንግተን ዲሲ በህወሀት ኤምባሲ ተከሽና በእነ ጃዋር መሀመድ ታውጃ፡ ሺዎች በደመነፍስና በስሜታዊነት የተቀላቀሉት ስለመሆኑ ከበቂም በላይ መረጃው አለኝ።
ለዛሬ መረጃዎቹን ላካፍላችሁ። ማስረጃዎቹን እየጠበኩኝ ነው። የድምጽና የፎቶግራፍ ማስረጃዎቹ ከእጄ እንደገቡ ጀባ እንደምላችሁ ከወዲሁ ቃል እገባለሁ። በእርግጥ አንድ ላይ ላወጣቸው ነበር እቅዴ። ሆኖም የጬሰው አቧራን እየቃሙ ላሉት ወገኖች በተወሰነ ደረጃ ሰከን እንዲሉ፡ ሰማይ ምድሩን የበጠበጠው ንትርክ የኦሮሞ ህዝብን ብሶት ለመግለጽ ታስቦ ሳይሆን በህወሀት መንደር ተዘጋጅቶ የቀረበ መርዛማ አጀንዳ መሆኑን በቶሎ እንዲያውቁት በሚል መረጃዎቹን ብቻ ላፈነዳቸው ፈለኩ። ሁለት ናቸው