Monday, September 30, 2013

የተቃውሞ ፓርቲዎች ሠላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባ

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 33ቱ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ለዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ክልከላ የአንድነት ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና መካሄዱ ተገለፀ።

Demonstration der äthiopischen Oppositions-Partei am 29.09.2013.
zugeliefert von: Lidet Abebe
copyright: DW/Y.G. Egziabher
የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሰልፉን ተከታትሎ ባደረሰን መረጃ መሰረት እጅግ በርካታ ሠላማዊ ሰልፈኞች ሠልፉን ለማከናወን ወዳቀዱበት መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ተከላክሎዋል። ከ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ጋ ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ ከድምፅ ዘገባው ያገኙታል።
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትኅ ፓርቲ ከ 33ቱ ፓርቲዎች ጋራ በመሆን ለዛሬ በመስቀል አደባባይ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በፖሊስ ክልከላ የአንድነት ጽ/ቤት በሚገኝበት ቀበና መካሄዱ ተገለፀ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ሰልፉን ተከታትሎ ባደረሰን መረጃ መሰረት እጅግ በርካታ ሠላማዊ ሰልፈኞች ሠልፉን ለማከናወን ወዳቀዱበት መስቀል አደባባይ እንዳይሄዱ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ተከላክሎዋል። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ በሰልፉ ወደ 80,000 የሚጠጉ ሰዎች መሳተፋቸውን የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እንደሚገምቱ ጠቅሷል። የዜና አውታሩ አያይዞም የመንግሥት ቃል አቀባይ ሬድዋን ሁሴን በሰልፉ የተገኙት በጥቂት መቶ የሚቆጠሩ እንደሆኑ መግለፃቸውንም ገልጿል።
Demonstration der äthiopischen Oppositions-Partei am 29.09.2013.
zugeliefert von: Lidet Abebe
copyright: DW/Y.G. Egziabher
አንድነት የጠራው ሠልፍ በከፊል
ሰልፈኞቹ የጸረ-ሽብር ሕጉ ይሰረዝ፣ የታሰሩ የኅሊና እስረኞች ይፈቱ፣ የኢሕአዴግ መገለጫው ሙስና ነው፣ የሕዝቡ የመሬት ባለቤትነት ይረጋገጥ፣ መብትን መጠየቅ አሸባሪነት አይደለም፣ ፍትኅ እንፈልጋለን፣ ዲሞክራሲ እንሻለን የሚሉና ሌሎች በርካታ መፈክሮችንም በከፍተኛ ድምፅ ማሰማታቸው ታውቋል።




በሰልፉ ላይ ከቃሊቲ እስር ቤት የተላከው የአንዱዓለም አራጌን ጨምሮ ዝዋይ ከሚገኙ እስረኞች የተላከ መዕልክት በንባብ ቀርቧል። ሠልፉ በአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር በዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ንግግር በፓርቲው ጽ/ቤት መጠናቀቁ ታውቋል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ልደት አበበ

ሰበር ዜና፣ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ!

September 29, 2013


ዛሬ ሴፕቴምበር 28 በኦስሎ ኖርዌይ ለግንቦት ሰባት ህዝባዊ ኃይል የታሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደረገ። በገቢ ማሰባሰቢያው ላይ በስጦታ እና ጨረታ ብቻ 408 ,633.85 የኖርዌጅያን ክሮነር የተገኘ ሲሆን ። ይህ ገቢ ከምግብ ሺያጭ ፣ ከመግቢያ ትኬት፣ ከቲሸርት ሺያጭ እንዲሁም ከተለያዩ ባህላዊ ቁሳቁሶች ሺያጭ ሳይጭምር መሆኑ ወዳጆችን ሲያስፈነድቅ ጠላቶችንን አንገት አስደፍቷል ። በፕሮግራሙ ላይ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እና ኮማንደር አሰፋ ማሩ በመገኘት ከሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያኖች ጋር ምክክር አድርገዋል። ሙሉ ዘገባውን በቅርብ ይዘን እንቀርባለን ።
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !
ከኖርዌይ
Norway G7 fundrise

Wednesday, September 25, 2013

Woyane got it all wrong; it has no way out but the unconditional surrender for democratic rule


September 24, 2013
The Ethiopian regime seems to misunderstand what the people of Ethiopia are demanding. The sooner the regime gets it and surrender peacefully for democratic rule the better it would be. Playing hide-and-seek game isn’t going to do it.  Spewing empty ethnic and religious propaganda isn’t going to save it. Hiding behind corrupt investments and empty growth propaganda isn’t a substitute for freedom. Tormenting the population and jailing the innocent with empty bravado isn’t going to help it form its inevitable demise. Woyane and its stooges must appreciate the tolerance of our people and accept the illegitimacy of the ruling regime and live with it. Noting will change that reality. 
by Teshome Debalke
Stupidity is a virtue brought about by ignorance, empty self-worth and bravado; oftenexhibited in a circle of people in-and around tyrannies, gangs and rouge groups that rely on intimidation and brut force to sustain their existence.  Therefore, the Ethiopian ruling regime known for its stupidity and brutality on the top of its organized corruption has no qualm to remain on the bottom of the pits since it came to power. Its apologists aren’t far behind; not willing to rise up to the occasion when the rotten regime reduces them to impersonator beyond recognition.

Monday, September 23, 2013

ኦሮማይ፣ ትግሉ በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ!


September 21, 2013

ከቴዎድሮስ ሓይሌ (tadyha@gmail.com)
ሠሞኑን የግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ስለ ኤርትራ ቆይታቸውና ስለድርጅታቸው ቀጣይ የትግል እንቅስቃሴ ሠፊ ገለጻና ማብራሪያ በኢሣት ቴሌቪዠን ከሠጡ ወዲህ የዘረኛው የትግሬ ነጻ አውጪ ግንባር ደጋፊ የሆኑት መርገማዊ ልሳኖች( አይጋ ፎረም ፤ ትግራይ ኦላይንና አውራንባ ታይምስ) እና አንዳንድ ተንበርካኪ የመንደር ሬድዮኖች ሰፊ የውግዘትና የህዝብን መንፈስ ያሸብርልናል በተቃዋሚዎችም ላይ ጥርጣሬ ይዘራልናል በሚል ደካማ ግንዛቤ እያካሄዱ ካለው አሰልቺና ኋላቀር ፕሮፓጋንዳ እጅግ ተጋኖ እየቀረበ ያለው ከሻብያ ጋር አብሮ መስራት ታላቅ የሃገር ክህደት ስለመሆኑ እፍረት የለሽ ኡኡታ በማሰማት ላይ ይገኛሉ።
Ato Andargachew Tsige, Ginbot 7
ይህንን ጽሑፍ እንድጽፍም ያነሳሳኝ ይህ የወያኔ በቀቀኖች ልቅ ያጣ የፀረ ሻብያ ውትወታ ወያኔ የምትባለው የጠባብ ዘረኞች ቡድን ለዚህ ዛሬ ለደረሰችበት የዘረፋና የልዕልና ደረጃ የበቃችው ከቶ በማን ትከሻ ሆነና ነው ። ዛሬ ሌሎች ኢትዮጽያውያን ወደ ኤርትራ ስለሄዱ ይህ ሁሉ ውንጀላ ደጋፊ ተብዬቹ የሚነዙት ወያኔ በሻብያ ሁለገብ ድጋፍ የማቴሪያል የትጥቅ የዕቅድና የሃሳብ መመሪያ ውጪ እንኳን ሚኒሊክ ቤተመንግስት ልትደርስ ቀርቶ ተከዜንም ባልተሻገረች ነበር።በአንድ ወቅት የኤርትራው መከላከያ ሚንስትር ጀነራል ስብሃት ኤፍሬም ስለ ወያኔዎቹ ያለውን እጅግ የወረደ ንቀት የገለጸበትን አባባል እንዳስታውስ አሰገደደኝ ‘’እኛ ከነጀነራል ደምሴ ቡልቱና ከነጀነራል ረጋሳ ጅማ ጋር በመዋጋታችን ኩራት‘’ የሚሰማን በመሆኑ ከነዚህ የፍየል እረኛ ወያኔዎች ጋር ፈጽሞ ለንጽጽር የማይቀርቡ እጃቸውን ይዘን ለዚህ ያደረስናቸው እኛነን ሲል ነበር ከአመታት በፊት የተናገረው። ወያኔዎች በሻብያ የበላይ ሹማምንት ብቻ ሳይሆን በተራው ተጋደልቲ ጭምር የሚናቁና እንደ ሻብያ አገልጋይ የሚታዩ ስለመሆናቸው ከሁለት አስዕርተ አመታት በኋላ እንኳ አለመለወጡን በረባው ባረባውም በባነኑ ቁጥር የሻብያ ስም እንደሚያስበረግጋቸው ዘወትር ከአፋቸው አለመጥፋቱን የምናስተውለው ሲሆን የሰሞኑ ደግሞ ተባብሶ የሚታየው ጫጫታ አንዱ የወያኔዎች የፍርሃት ማሳያ ይመስለኛል።

Ethiopia: Beyond the Hubris of Evil

September 22, 2013

When I wrote a commentary on the plight of the imprisoned 32-year old Ethiopian journalist Reeyot Alemu last April, I titled it “The Audacity of Evil in Ethiopia.” At the time, the Committee to Protect Journalists (CPJ) had sent a letter to the “Minister of Justice” of the ruling regime in Ethiopia pleading medical care for Reeyot and urging them to spare her from a threatened solitary confinement. In that commentary, I explained why I was compelled to “stray from my professional fields of law and politics” to moral philosophy.
Reeyot began a hunger strike to protest an order by regime officials
In this commentary, I am again compelled to indulge in philosophical musings on the hubris of evil. I am prompted once again by a statement of the Committee to Protect Journalists issued last week protesting the decision by the ruling regime to impose severe visitor restrictions on Reeyot.  CPJ “called upon the Ethiopian authorities to lift these latest restrictions and allow Reeyot Alemu to receive all visitors… She is a journalist, not a criminal, and should not be behind bars.”

Friday, September 20, 2013

ወያኔም በስደት (ጌዲዮን ከኖርዎይ)


September 20, 2013

ጌዲዮን (ከኖርዎይ)
መቼም እንደወያኔ አገዛዝ ስደት የሰፈነበት የኢትዮጵያ ታሪክ የለም፥፥ ምሁራን፥ ተማሪ፥ ሰራተኛ፥ የሃይማኖት አባቶች፥ ገበሬው፥ ወጣት ወንድሞችና እህቶች፥ ብቻ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተሰዷል፥ አሁንም በመሰደድላይ ነው፥፥ ብዛት ያላቸው ወንድሞችና እህቶቻችንም ከተሰደዱ በኋላም ወይ መንገድ ላይ ወይ ሰው ሃገር ከገቡ በኌላ ህይወታቸውን ያጣሉ ይሰቃያሉ፥፥
በመላው አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከገዛ ሃገራቸው በወያኔ/ህወሃት አፋኝ ስርአት በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ፥የዲሞክራሲና የነፃነት እጦት፥ የዘረኝነት መስፋፋት፥ የህግ የበላይነት አለመከበር፥ የኑሮው ከአቅም በላይ መሆንና በሌሎችም በበርካታ ምክንያቶች በግፍ ከገዛ ሃገራቸው ተሰደው ከወጡ በኋላ በሚኖሩበትን ሃገር የመናገር የመፃፍና ሃሳባቸውንበነፃ የመግለፅ መብታቸውን በመጠቀም፥ የወያኔ መንግስትንእኩይ ተግባር ለማጋለጥ ይሞከራል፥፥ ይሁንና ይህ እንቅስቃሴ የወያኔ ማህበርን እንቅልፍ እንደሚነሳ ደሞ አያጠያይቅም፥፥
በዚህም ምክንያት ሃገር ቤት ሃሳባቸውን በድፍረት መግለፅ የቻሉት በሙሉ ማለት ይቻላል አሸባሪ የሚል ቅፅል ስም ተለጥፎባቸው በየእስር ቤቱ በማጎር ሰዎችን ለማፈን ቢሞከርም ኢትዮጵያ ደሞሁል ግዜ ሰው አላትና ተተኪው ብቅ ማለቱ አቀረም፥፥ ወደውጩ ልመለስና የዲያስፖራውን ኢትዮጵያዊ ምን ሊያረጉት ይችላሉ አይሉኝም፥

Ethiopian Women’s Human Rights Alliance (EWHRA) Submits Human Rights Report on Ethiopia to the United Nation’s


September 19, 2013
Ethiopian Women’s Human Rights Alliance
For Immediate Release
September 19, 2013
Contact Information:
Email: voiceofethiopianwomen@gmail.com

Ethiopian Women’s Human Rights Alliance (EWHRA) Submits Human Rights Report on Ethiopia to the United Nation’s Universal Periodic Review
Grassroots organization details human rights violations committed by the Ethiopian government and outlines recommendations to bring Ethiopia into compliance with international law.
New York, New York—Ethiopian Women’s Human Rights Alliance (EWHRA) released a report today submitted to the Universal Periodic Review (UPR), a United Nations (UN) mechanism aimed at reviewing the human rights record of UN member countries. EWHRA’s report details the egregious violation of human rights committed by the Ethiopian government in contravention of its obligations under numerous international human rights treaties.

Monday, September 16, 2013

የመስከረም 12 ሰልፍ በታቀደለት ጊዜ ይካሔዳል (ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ማገለጫ)

September 16, 2013

.
የመስከረም 12 ሰልፍ በታቀደለት ጊዜ ይካሔዳል!!!!!
ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሊያካሂደው የነበረው የተቃዉሞ ሰላማዊ ሰልፍ በመንግስት ታጣቂዎች ህገ ወጥ እርምጃ ከተደናቀፈ በኋላ ነሐሴ 3ዐ ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ፓርቲው መስከረም 12 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ሰላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል እንዲያውቀዉ አድርጓል፡፡ ይህንን ተከትሎ የሰላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሣወቂያ ክፍል ጳጉሜ 1 ቀን 2ዐዐ5 ዓ.ም. በተጻፈ ደብዳቤ የሰለፉን ዓላማ፣ የሰልፉ ተሳታፊዎች የሚጓዙበትን መስመርና የሰልፉ መዳረሻ ከግንባታ ስራና ከፀጥታ ጥበቃ ጋር ያለውን ችግር አስመልክቶ ማብራሪያ እንደሚያስፈልግ በጠየቀዉ መሠረት፡-
Blue Party Ethiopia
1ኛ. የሰልፉ ዓላማ፤
በህገ መንግሥቱ የተደነገጉት ሃሣብን በነፃነት የመግለፅ መብት እንዲከበር፣ዜጐች በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተዘዋውሮ የመሥራትና ሀብት የማፍራት መብታቸው እንዲከበር፣ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 11፡3 በግልፅ የተደነገገው መንግሥት በኃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ኃይማኖትም በመንግሥት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም የሚለው ድንጋጌ እንዲከበር፣ መንግሥት የኑሮ ውድነትና ሥራ አጥነትን ለመቅረፍ የፖሊሲ ማሻሻያ እንዲያደርግ የሚሉትን ጥያቄዎች በሰላማዊ ሠልፍ መንግሥትን ለመጠየቅ መሆኑን፤

“ሌኒን : ትሮተስኪ : ስታሊን” ከ “መለስ : አርከበ : አባይ”


September 14, 2013

© Abraha Desta
Source:- Face book from Abraha Desta timeline.
tplf rotten apple
(ፅሑፉ የማን እንደሆነ አላወቅኩም። አንድ የፌስቡክ ጓደኛዬ የላከልኝ ነው። የአፃፃፍ ጥበቡና ቁምነገሩ ስለማረከኝ እነሆ ለጠፍኩት፤ የአፃፃፍ ስልቱ ግን የተስፋዬ ገብረአብ ይመስላል። ለማንኛውም መልካም ንባብ)
የቦልሸቪኩ መሪ ሌኒን በጣም የሚታወቅበት በዲሞክራሲ ማእከላዊነትና በተለያዩ ሰዎች የሚታወቁ ንድፍ ሃሳቦችን በራሱ መንገድ በመናገሩና በማሳመኑ ነው:: በፖሊት ቢሮው ውስጥ እጅግ በጣም ልቅ የሆነ ክርክር ሲያደርጉ አብዛኛው ግዜ ወጥሮ የሚይዘውና እስከ መሸነፍም የሚደርሰው የአብዮቱ አጋር የሆነው ትሮተስኪ ነበር:: ትሮተስኪ ከሌኒን በላይ የማሳመን ችሎታ ያለው እንዲሁም ሲበዛ ዲሞክራት ነበር:: የሌኒን ፍስፍና ተንኮል የበዛበት ሲሆን አብዛኛው ግዜም የራሱ አዲስ ሃሳብ የቀድሞ የኢኮኖሚክስ ፈላስፋዎች ነው እያለ ለፖሊትቢሮው ያቀርብ ነበር ፤ ይህ ያደረገበት ምክንያትም የራሴ ሃሳብ ነው ካለ ቶሎ አይቀበሉኝም ያንቋሽሹብኛል በማለት ነበር:: ሌኒን የብሄር ችግርም ስለነበረው የሚያደርገው እንቅስቃሴ ስልጣኑን የሚያደላድልበት አዃኋን ነበር:: ሌኒን ያ ሁሉ የዓምስት ዓመት መርሃ ግብር አለኝ እያለ ሳይወድ ለዘልአለሙ አሸለበ:: ሌኒን በካድሬዎቹ አማካኝነት በሕዝቡ ዘንድ በጣም እንዲወደድና እንዲከበር አድርጓል:: 

Friday, September 13, 2013

” እኔ ባልፍም እንኩዋን ሺህ ርዕዮቶች ስላሉ በርቱ አትደናገጡ “

September 12, 2013

Sources:-  Daniel Haregawi Timeline(FB)
ke  Sekedar alemu
Reeyot-Alemu


* የርዕዮት ደህንነት አደጋ ላይ መሆኑን እንድታዉቁት ስል ነዉ ይህንን በብዙ ሀዘን ዉስጥ ሆኜ የጻፍኩላችሁ
ትላንትና እንደሁል ጊዜዉ ስንቅ ይዤላት ወደ ቃሊቲ ሔድኩ በር ላይ ያለዉ ፖሊስ “የርዕዮት እህት ነሽ አይደል እሱዋን መጠየቅ አትችይም በአስተዳደር በኩል ሔደሽ ጠይቂ” አለኝ፡፡ እንዳዘዘኝ በአስተዳደር በር በኩል ሔድኩ ወደ ዉስጥ በስንት ትግል ከስለሺ (የርዕዮት እጮኛ) ጋር ገባን፡፡
ከብዙ ጥበቃ በሁዋላ በብዙ ፖሊሶች ታጅባ መጣች ፊትዋ ተለዋዉጦ ስለነበር ምን እንደሆነች ስጠይቃት ከእናት፡ አባት እና ንስሃ አባት ዉጪ ማንም ሊጠይቃት እንደማይችል እና የእነሱን ስም እንድትሰጥ እንደተጠየቀች እና አሚናዘር የሚትባል የሴቶች ክፍል ሀላፊ አልጋዋ ድረስ በመምጣት እንደሰደበቻትና እንደዛተችባት እየነገረችኝ እያለ አሚናዘር የተባለችዉ ሃላፊ ወደኛ በመምጣት ርዕዮትን በማመናጨቅና በመስደብ ከኛ ልትወስዳት ስትሞክር ለምን እንደሆነ ስጠይቃት “ከዛሬ ወዲህ ዐይኑዋን አታዩትም ማንም እኔን ሊያዝ አይችልም የእናንተ ጋዜጣና ሚዲያ ምን እንደሚያመጣ እናያለን ” በማለት ርዕዮትን በማዋከብ እና በመጎተት እየሰደቡ ወሰዱዋት፡፡ ምድር ላይያሉ ሰቅጣጭ እና ለህሊና የሚከብዱ ስድቦችን አወረዱብን በዚህ መሀል ርዕዮት ድምጹዋን ከፍ አርጋ “የማልጨርሰዉን ነገር አልጀምርም እኔን ለማንበርከክ እና ለማሸማቀቅ ክሆነ መቼም አላረገዉም ትገይኝም ከሆነ ነይ ተኩሺ ” ስትል ጎትተዉ ወሰዱዋት፡፡ እኛንም ከጊቢዉ አዋክበዉ አስወጡን፡፡