Saturday, February 22, 2014

የኢትዮጵያን ገጽታ አደባባይ ያወጣው አውሮፕላን አብራሪ ሃይለመድህን አበራ


February 22, 2014
ዳኛቸው ቢያድግልኝ
ልማታዊ ግስጋሴ እስከ ግድበ ህዳሴ በደረሰበት ታሪካዊ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በፈጣን የእድገት መስፈርት ውስጥ ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም ከቻይና ቀጥሎ ሁለተኛ ነች እየተባለ በመሪዎቿ በሚነገርላት ጊዜ። አሸባሪዎችን ከመነሻቸው ለማምከን በአይነቱ ልዩ የሆነ የአንድ ለአምስት አደረጃጀት የሰዎችን ድርጊት ብቻ ሳይሆን አስተሳሰብን ጭምር የሚመረምር ምትሃታዊ ሃይል ተደራጅቶ ባለበት ሁኔታ የዴርቶጋዳን ልብወለድ መሰል ነገር መታየቱ ብዙዎችን አስደምሟል። ለመሆኑ የዛሬ ልጆች ጀግና አይደሉም የሚል ማን ነው?
በውጭ ሃገር የዜና ማሰራጫዎች ወሬው እንደተሰማ አስተያየት ለመክተብ ጣታቸው እንደ ክላሺኒኮቭ ፊደል የሚያንጣጣ ሁሉ ፓይለቱ ጥገኝነት ለማግኘት ብሎ እንዲህ ማድረጉ አሳፋሪ ነው፣ አላዋቂ አፍሪካዊ መሆን አለበት፣ ይቀጣ! ይቀጣ! የሚሉ ሃረጎች በርክተው ነበር። እነዚህ በአብዛኛው አፍሪካ ማለት አንድ ሃገር የሚመስላቸው የእውቀት ብርሃን የጨለመባቸው ናቸውና ምንም ማድረግ አይቻልም።
Ethiopian Airlines plane Co-Pilot Hailemedehin Abera Tagegn.
ሁለተኛው ሰሞኑን ነገረ ስራው አያምርም ነበር የሚልና አእምሮው ለየት ያለ ነገር የሚያሳየው ‘ሺዞፍሬንያ’ እሚሉት ነገር እየጀማመረው ነበር የሚለው ነው። እህት ሁሉም ይስማልኝ በማለት በመረጃ መረቦች በተነች የሚባለውን ያነበበ ሰው ለበረራ ብቁ ነው የሚለውን ፈቃድ ሰጪም ወፈፍ ያደረገው መሆን አለበት ቢል አላጋነነም። ይሄ እብድ እየመሰለ ሲሰልል የኖረ ወያኔ ወፈፌነትን በጣም ስለተለማመደው አማኑኤል ሆስፒታልን የደህንነት ማሰልጠኛ ኮሌጅ አድርጎ ቢመለከት አይፈረድበትም ብለን መሳቅም መብታችን ነው። ቁም ነገሩ ግን የበረራውን ደህንነት ለማስጠበቅ የአብራሪዎችንምጤናና ደህንነት መከታተል ስለሚገባው ያንንም ማድረግ ባለመቻሉ ወደ ትልቅ ስህተት ራሱን እየጨመረ ነው። በዚህ ሁኔታ ምን  ያህል ወፈፌ ፓይለቶች ይኖሩ ይሆን ብሎ መጠየቅም ያስፈልጋል። ከሆነም ምን አይነት አስተዳደር ቢኖር ነው ጨርቅ ጥሎ የሚያሳብደው፣ ሃገር ጥሎ የሚያስኮበልለው ብሎ መጠየቅም ተገቢ ነው። የአይጥ ምስክሯ ድንቢጥ እንደሚባለው በአንድ-ለአምስት ተጋግዞ መዋሸት ይቻል ይሆናል ከዚያ መረብ ውጪ ላለነው ግን አስቂኝ ትዕይንት ነው።
እኔ አውሮፕላኑን ጠለፈ የሚለው አገላለጽ እጅግም አልተመቸኝም።  ረዳት አብራሪው ድምጼ ይሰማልኝ በማለት ማቆም የማይገባው ስፍራ ላይ አውሮፕላኑን አቆመ ለዚያውም ያለ ፍርሃትና ሽብር መደናገጥና መርበትበት ተሳፋሪውም ኮሽታ ሳይሰማ። አቅጣጫ በቀየረው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ሰራተኞች ለተሳፋሪዎቻቸው ቡና ሻይ እያቀረቡ ምቾታቸውን እየጠበቁ ዋናው አብራሪ ጋዜጣቸውን እያነበቡ ምቾታቸው ሳይጓደል አረፉ። ተሳፋሪዎች የሆነውን ሁሉ ሳያዩ ረዳቱ አብራሪ በገመድ ወርደው ለፖሊሶች እጃቸውን ሰጡ። እንግዲህ የአእምሮ በሽተኛ እንደዚህ ከሆነ ተጋግዘን ብንታመምስ ምን ነበረበት?

Wednesday, February 19, 2014

ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው – ከዚያስ?


“ኢህአዴግ የተጭበረበረ ሪፖርት አቅርቦ” ነበር
world bank foto


ኢህአዴግ “አልመረመርም፣ አልበረበርም” በማለት ሲያንገራግር ከቆየ በኋላ በዓለም ባንክ ቀጭን ትዕዛዝ ለመበርበር መስማማቱን ገልጾ በተለያዩ አካላት ምርመራ ተካሂዶበታል። በተከታታይ ሲካሄድ የነበረው ምርመራ አካል የሆነው የመጨረሻ ምርመራ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተጠናቋል። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች እንደተናገሩት ስድስት አባላትን ያካተተው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ኢህአዴግን መርምሮ ተመልሷል። የሚጠበቀው የመጨረሻው ሪፖርትና ሪፖርቱ የሚቀርብለት የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ነው። በቅርቡ የሚወጣውን ውሳኔ አቅጣጫ ለማስቀየር በማሰብ ኢህአዴግ ለመርማሪው ቡድን ራሱ የፈጠረውን “የተጭበረበረ ሪፖርት” አቅርቦ ነበር፡፡
ኢህአዴግ ምርመራውን በተቀነባበረ የፈጠራ ሪፖርት ለማምለጥ ሞክሮ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጮች “የመርማሪዎቹ ቡድን ሪፖርቱን አንቀበልም፣ የችግሩ ሰለባዎችና ክሱን የመሰረቱት ክፍሎች በሚኖሩበት ቦታ በመገኘት ነዋሪዎችን በተናጠል ለማነጋገር እንፈልጋለን” በማለት ኢህአዴግን እንደሞገቱት አስታውቀዋል። ኢህአዴግ በልማትና በህዝብ ስም የሚያገኘውን ከፍተኛ የዕርዳታ ገንዘብ የጦር ሃይሉን ለማደራጀት፣ የደህንነትና የፖሊስ ሃይሉን ለማስታጠቅና ርዳታ በሚለመንባቸው ዜጎች ላይ የተለያየ ወንጀል ፈጽሟል፣ አሁንም እየፈጸመ ነው በሚል መወንጀሉ ይታወሳል።
የምርመራው መነሻ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በቀድሞው ጠ/ሚኒስትርና የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ፣ የህወሃትና የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝና በየደረጃው ያሉ አስፈጻሚዎች በጋምቤላ ክልል የተከናወነው የጅምላ ጭፋጨፋ ነው። በወቅቱ የተካሄደው ጭፋጨፋ ከ400 በላይ የተማሩ የአኙዋክ ወንዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ዓለም አቀፋዊ ሪፖርቶችና የጉዳዩ ሰላባዎች ይፋ ያደረጉት ጉዳይ ነው። አቶ መለስ ሞት ቀደማቸው እንጂ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀረበባቸውን የክስ ማስረጃ ተቀብሎ ክስ እንዲመሰረትባቸው ከድምዳሜ መድረሱም ይፋ ሆኖ ነበር። ኢህአዴግ በዚሁ ፍርድ ቤት ላይ የአፍሪካ መሪዎችን የማስተባባርና የፍርድ ቤቱን አካሄድ ማውገዝ የጀመረው አቶ ኦባንግ የሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አቶ መለስ ላይ የመሰረተው ክስ እንዲከፈት መወሰኑን ተከትሎ እንደሆነ በወቅቱ ከየአቅጣጫው አስተያየት የተሰጠበት ጉዳይ ነው።

Thursday, February 13, 2014

በሳንሆዜ ከተማ ለወራት የታቀደው የወያኔ የማጭበርበር ሴራ በሚያሳፍር መልኩ ተጠናቀቀ


February 12, 2014
የሳንሆዜ ሀገር ወዳዶች ግብረሃይል
እራሱን የአባይ ግድብ ካዉንስል ብሎ የሚጠራው የወያኔ ስርጎ ገቦች እና የባንዳወች ቡድን ለወራት ለወያኔ ቱባ ባለስልጣናት እጅ መንሻ የሚሆን ገንዘብ የማግኛ ዘዴ ላይ መዶለት እንደጀመረ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን ወዲያውኑ ውጥኑን ስላወቅን በመሃከላቸው ሰርጎ በመግባት እያንዳንዶን እቅዳቸውን ስንከታተል ቆይተናል። የሴራው ዋንኛ የባንዳነት ሚና ተጫዋቾች ቀድሞውንም ለወራሪው የኢጣልያ ጦር እንቁላል አቀባይ ከነበሩ ቤተስብ የበቀሉ መሆናቸውን ስንረዳ ደግሞ ልባችን በሃዘን ደምቶል።በጣሊያን ወረራ ዘመን ድልድይና ህንጻ በመሰራቱ ወራሪው ጦር ይግዛን ያላለውን እና ነጻነቱን ያስቀዳመውን ህዝባችን ዛሬ የወያኔ ደናቁርት ካድሬዎች በህዝብ ጠኔ የትላልቅ ህንጻ ባለቤት እና የባለዘመናዊ ተሽከርካሪ ባለቤት መሆናችው ያደባባይ ሚስጥር ሆኖ ሳለ፤ ላለፉት ሃያሶስት አመታት የህዝባችን ኑሮ ከድጡ ወደማጡ ማምራቱ እየታወቀ ‘’ልማታዊ’’ የሚል ጭምብል ለብሰው ለማደናገር መሞከራቸውን  ከጅምሩ በቁጭት ተከታትለናል።
Ethiopian community in San Jose
ሴራው ወደ ተግባር የሚለወጥበት እለት እንደደረስም በከተማው የምንኖር ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሃይማኖት፤ቋንቋ እና የብሄር ልዩነት ሳይከፋፍለን የእምነት እዳ የሆነውን እና በቃልኪዳን የወረስነውን ስንደቃችንን በማንገብ በቦታው ተገኝተን ካሃዲዎችን ተቃውመናል። ካአባይ በፈት ስብአዊ መብትን መገደብ ይገደብ ፤ ወያኔ ከፋፋይ ነው ፤ ወያኔ ህዝባዊ ውክልና የለውም፤ አላግባብ የታስሩ የሃይማኖት እና የፖለቲካ እስረኞች ካለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ፤ ሌሎችንም መፈክሮች በማሰማት እና መዝሙሮችን በመዘመር የተነቃቃ እና የሚያስደንቅ ወኔ የተላበስ ጨዋነታችን አሳይተናል።
በሃገር ወዳዱ ተቃዋሚ ወኔ ልባቸው የራደው የወያኔ ጀሌዎች ባለ አራት ስኮድ የፖሊስ ሃይል እና ከአስር በላይ የግል ጸጥታ ስራተኞች በማስመጣት ግቢውን ለማጠር ቢሞክሩም ኢትዮጵያዊ ጨዋነትን የተላበሰው ተቃዋሚ ሃገር ወዳድ ለጸጥታ ሰራተኞች ህግ አክባረነቱን በማሳየት መብቱን ግን ሳይነጠቅ ድምጹን አሰምቶል። ተቃወሞውን ከሰአት በሆላ በስምንት ሰአት ግድም የጀመረው ሃገር ወዳድ እስክ ምሽቱ ሁለት ስአት በቦታው የተገኘ ሲሆን ጨለማን ተገን አድርገው ከገቡ ባንዳዎች በተጨማሪ በወያኔ ጉዳይ አስፈጻሚነት የሚታወቁ ክሃዲወች ፤ ስለ ወያኔ አንጻራዊ ግልጽነት የሌላቸው ወይንም ከወያኔ ህልፈት በፊት ድርሻቸውን መውስድ የሚፈልጉ ባእዳን ተደምረው ከ40-50 ያልበለጡ ሰዎች ተገኝተውበታል።

የአዲሲቱ ኢትዩዽያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ የ3 ቀን ቆይታ በኖርዌ


February 12, 2014
የሺሀረግ በቀለ (ኖርዌ)
Obang Metho in Norway
ተወዳጁ የሰብአዊ መብት ተከራካሪና የአዲሲቱ ኢትዩጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በ8-2-2014 በኖርዌ ኦስሎ በመገኘት ከኢትዩዽያዉያን የስደተኞች ማሕበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር በኖርዌ ስለሚገኘው ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮዽያዊ የሰብ አዊ መብት አያያዝ ሁኔታ እና ይህ ጥገኝነት ጠያቂ በኖርዌ ምን ያህል ተቀባይነት አለው በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል።
በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ9-2-2014 በሳውድ አረቢያ የተጎዱ ኢትዩጵያውያን ወገኖቻችንን ለመርዳት በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እኛ ስንሰቃይ አሜሪካ ዝም ብላ ይሆናል ፣እኛ ስንሰቃይ የአውሮፓ ሕብረት ምንም አላለ ይሆናል የኢትዩጵያ አምላክ ግን ከኛ ጋር ነው በሚል ልብ የሚንካ ነገር ተናግረዋል።
በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ10-2-2014 በኖርዌ ጥገኝነት በጠየቁ ኢትዮዽያዊ ወገኖቻቸው ላይ ስላለው የሰብ አዊ መብት አያያዝ እና ምን ያህል ጉዳያቸው እየታየ ነው የሚለውን በማንሳት ከLandinfo እና NOAS(norsk organisation for asylsøkere) ጋር በሰፊው ውይይት አርገዋል።

Tuesday, February 11, 2014

ሰው ለሆኑ ሰዎች በሙሉ! (በጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፤ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት)


February 11, 2014

የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡

‹‹ይህንን ስለመሳሰሉ ጉዳዮች መወያየት ክልክል ነው፡፡›› በማለት በተንጎላጀጀ ድምፅ ጠባቂው ተናገረ፡፡ ቀጠል አደረገናም ‹‹መነጋገር የምትችሉት ስለቤተሰብ ጉዳዮች ብቻ ነው›› በማለት ተናገረ፡፡ ይህን ከላይ ያለውን ሐሳብ የሚመለከት ማንኛውም አንባቢ፣ ጉዳይ የተፈፀመው እዚህችው እማማ ኢትዮጵያ ሰማይ ስር ባሉ አጃኢበኛ እስር ቤቶች፣ ቤተሰብ መጠየቂያው እንደሆነ መጣራቱ አይቀርም፡፡
Ethiopian journalist Woubshet Tayemes journalist
ይሁንና በመግቢያው ላይ ያለው ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ‹እናት› ከተሰኘውና እ.ኤ.አ. በ1906 ከታተመው የስመ ጥሩው ሩስያዊ ደራሲ ማክሲም ጎርኪይ ታሪካዊ ልቦለድ ገፅ 102 ላይ ነው፡፡ የዛሬ 108 ዓመት አካባቢ ማለት ነው፡፡ አቤት ርቀቱ!… ይህ ርቀት ግን ለእኛ ምንም ማለት ያልሆነ ይመስላል፤ ለምን? ቢሉ ዛሬም ይህንንና ይህን የመሳሰለውን አስፍተን እየሠራን እንገኛለን፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ሁኔታዎች እየተጓዝን ያለነው የቁልቁለት ሩጫ በእጅጉ አሳሳቢ ሆኖ ይገኛል፡፡
የነገሮች ሁሉ መድረሻ እስር ቤቶች እየሆኑ መጥተዋል፡፡
‹ጠበቅ ያለ እርምጃ፣ የማያዳግም እርምጃ፣ የማስወገድ እርምጃ፣…› ወዘተ የሞሉ ከሕግ መርሕዎች ሳይሆን ከጥላቻ ፖለቲካ የሚመነጩ ፀያፍ አነጋገሮችን በሕዝብ የመገናኛ ዘዴዎች ሲተላለፉ እየሰማን እየታዘብን ነው፡፡ ቃል በቃል ‹ቀይ ሽብር ይፋፋም› ብሎ ማወጅ የቀራቸው የሕግም የግብረገብም ሚዛን ያልወጣላቸው ቀረርቶች በተለይ በእስር ቤት የምንገኝ ኢትዮጵያውያንን እየሰበሰቡን ይገኛሉ፡፡
ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት›
በኢ.ቴ.ቪ. የአብዮታዊ እርምጃ ፕሮግራሞች በቀረቡ ማግስት አሁን በዝርዝር ብለው የብዙ ቤተሰቦችን ስሜት ሊያሸማቅቁ የሚችሉ ሰቆቃና እንግልቶች በአስደማሚ ስልት ተቀናብረው ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡ እስኪ የተወሰኑትን እንይ፡፡ ማንኛውም ታሳሪ ቤተሰብ በቅርብ ሊጎበኘው በሚችለው እስር ቤት ይታሰር የሚለው ሕግ የተሻረው በእኛ ላይ ነው፡፡ ዝዋይ የአገራችን ‹ሳይቤሪያ ግዞት› ማለት ናት፡፡ ቤተሰብ ያን ያህል የበርሃ ጉዞ አቋርጦ የእኛዋ ሳይቤሪያ ሲደርስ በአድካሚና ግብረ-ገብ በጎደለው ፍተሻ መከራውን ማየቱ አንሶ ጆሮ ግንዱ ላይ በቆሙ የቤተሰብ አገናኞች ቤተሰባዊ ገመናውን አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሕፃናት ልጆች ወላጆቻቸው አንድ ላይ ሆነው ናፍቆታቸውን መወጣት አይችሉም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ፖሊሶቹ ሲዘናጉልን ልጆቻችንን አቅፈን እንስማለን፡፡ ይህ ከሆነ ቁጣና ዘለፋው ምንም አይደለም፡፡ ግን በሁኔታው ሕፃናቱ ክፉኛ ይበረግጋሉ፣ የእኛ ስጋት ይጋባባቸዋል፤ በዚህም መንፈሳቸው እርብሽብሽ ብሎ ወደቤታቸው ይመለሳሉ፡፡

Sunday, February 2, 2014

Live blogging: Gonder, Meskel Square Rally


February 2, 2014
በጎንደር መስቀል አደባባይ በከፍተኛ ድምቀት ሲካሄድ ያረፈደው ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠናቋል።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር የተፈጸመው ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ፣ በአይነቱ በጎንደር ያልተለመደ ነው።
ሰማያዊ ፓርቲ የጎንደር ህዝብን አስተባብሮ ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ወያኔ በሚስጥር ከሱዳን መንግስት ጋር ተደራድሮ መሬት ለሱዳን አሳልፎ መስጠቱንና ወደፊትም ተጨማሪ መሬት ለመስጠት በመዘጋጀት ላይ መሆኑን የጎንደር ህዝብ ግንዛቤ እንዲኖረው አድርጓል።
የወያኔ ባለስልጣኖች የሰማያዊ ፓርቲ በፈጠረው ጫና ምክንያት ሰሞኑን በሚስጥር ሲያካሂዱት ስለ ነበረው የመሬት ማካለል ጉዳይ በሚቆጣጠርዋችው ሚድያዎች መናገር ጀምረዋል።
Semayawi party Gonder demonstration
Semayawi party Gonder Demo picture
****
00:00
00:00
****
*በአሁኑ ሰዓት ECADF ወደ መስቀል አደባባይ እየተጠጋ ካለው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ጋር የቀጥታ የስልክ ግንኙነት አለው… ቡድኑ አደባባዩ ሲደርስ ሁኔታውን በቀጥታ ይከታተሉ።
****
*የጎንደር ህዝብ ሰማያዊ ፓርቲ የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ለመቀላቀል ወደ መስቀል አደባባይ እየጎረፈ ነው።
*የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ጎንደር ገብተው ወደ ህዝቡ እየተቀላቀሉ ነው ::

ሌንጮ ለታ – ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…?


February 2, 2014
ክንፉ አሰፋ
Former OLF chairman Lencho Leta
ኦቦ ሌንጮ ለታ
ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። “ወጣ ብለው ይግፉ።”  ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት።  ”ይግዙ” ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ መኪና መግዛት ይቀላቸዋል።  የቤቶች ድራማ ላይ እከ ደከ አስር ጊዜ “እኔን ነው?” የሚለው ወዶ አይደለም። ማመን የሚቸግሩንን ነገሮች ማጣራት ስንፈልግ እንደጋግማለን።
በዚያን ሰሞን በኦቦ ሌንጮ ለታ የወጣው ዜና ብዙዎችን አስገርሟል።
“ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን።” የሚል ነበር የዜና እወጃው ርዕስ። ይህን ርዕስ እንዳየሁ አይኔን በደንብ ጠረግ ጠረግ አደረግኩና እንደገና አነበብኩት።
“ታሪክ እንሰራለን” የሚለው ሃረግ በስህተት የሰፈረ ነበር የመሰለኝ።  ሌንጮ ለማለት የፈለጉት “ታሪክ እናነባለን” ይሆናል በሚል ጥርጣሬ ደጋግሜ ያየሁት።  ያነበብኩት ነገር ትክክል ነው። ይህንኑ ቃል ከራሳቸው አንደበትም ሠማሁ።  በስህተት የሰፈረ ዜና አልነበረም።  ታሪክን ማንበቡም ሆነ መስራቱ ቀርቶ “ሃገር ቤት ገብተን አዲስ ታሪክ እንጽፋለን።” የሚል ቢሆን እንኳን ግርታውን ይቀንሰው ነበር።
በፍትህ ሳይሆን ይልቁንም በአዋጅ በምትተዳደር ኢትዮጵያ፤ እጅና እግራቸውን ብቻ ይዘው በመግባት ታሪክ መስራት የሚችሉ ከሆነ በምትሃት አልያም በመለኮታዊ ሃይል ብቻ መሆን አለበት። ሌንጮ ሃገር ቤት ገብተው ሰላማዊ ትግል ለማድረግ መወሰናቸው ላይ ምንም ችግር የለብኝም። የዚህ ውሳኔ ትክክለኝነት የሚዳኘው አስቀድመው በሚተቹ እና በሚተነብዩ የፖለቲካ ነብያት አይደለም። ፍርድ የሚሰጠው ሂደቱ በተግባር ሲፈተን ብቻ ይሆናል። ይህን ለማየት ደግሞ ብዙም ሩቅ አይሆንም።  በጎረበጠ የፖለቲካ መንገድ ላይ ጉዞ ለማድረግ ወደ ሃገር ቤት ለመግባት መወሰናቸው ግን አስመራ ላይ፤ በሻእቢያ ከታገቱት የኦነግ መሪዎች የተሻለ ውሳኔ ይመስላል።  ታሪክ ለመስራት አስመራ የመሸጉት እነ ዳውድ ኢብሳ ታሪክ ሆነው ቀርተዋል።