Sunday, March 2, 2014

ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ)


March 2, 2014
ከፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ
አንድ ጥናት ሳነብ፥ ምናልባት እናንተም አንብባችሁት ይሆናል፥ የተፈጥሮ ሀብት ባላት ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከተራቡ፥  የማሰብ ችሎታቸው ዝቅተኛ ቢሆን ነው ሲል አገኘሁት። “ጥልቀት የሌለው ረጋ-ሠራሽ ጥናት ነው” ብዬ ጣልኩት። የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ባለጠጋ መሆኗን እርግጥ ባለሞያዎች የመሰከሩት ነው። ማዳበሪያ የማያስፈልገው መሬት ታርሶ አያልቅም። የወንዞቿ ውሀ ለጎረቤት አገሮች ሳይቀር ይተርፋል። ይኸንን እውነታ በቀጥታ ከተመራማሪዎቹ  አፍ ለመስማት የፈለገ ፕሮፌሰር ስዩም ገላየን ማዳመጥ ይችላል
Prof Getachew Haile Ethiopia
እንዲህ ከሆነ፥ ትኩረቱ በኢትዮጵያውያን የማሰብ ችሎታ ላይ ሊሆን ነው። እውነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ተመጽዋች ሆኖ የቀረው የማሰብ ችሎታው ዝቅተኛ ሆኖ ነው? አይመስለኝም።  ሰውየው ጥናቱን ማስተካከል አለበት። አለዚያ፥ ከዚያ ቀጥሎ፥ “አንድ ሰው እሱቁ ውስጥ ከመስተዋቱ በስተኋላ ድፎ ዳቦ እያየ ከተራበ የአስተሳሰብ ችሎታው ዝቅተኛ ቢሆን ነው” ሊለን ነው። ምንም ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ ቢኖረው፥ ዳቦውን እንደማያገኘው ለማንም ግልጽ ነው።
እርግጥ ነው፥ በአስተሳሰብ ደከም የሚል ሰው ሊጎዳ ይችላል። ሌላው ቢቀር፥ የብልሁ ጓደኛውን ያህል አይደላውም።  ግን በከፍተኛ ደረጃ የማሰብ ችሎታ ያለው ሰውም ሊቸገር ይችላል።  ስንቶች ናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በችግር የሚኖሩ፥ መውጫ ቢያገኙ ግን ለሌላው ሳይቀር የሚተርፉ? በአፍሪካ፥ በአውሮፓ፥ በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በማስተማርና በምርምር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቊጥር ቀላል አይደለም። በንግዱ ዓለምም ቢሆን፥ “የሺ ብር ጌቶችን” ጓዳ ይቊጠራቸው።
የለም፥ የተፈጥሮ ሀብት ባለጠጋ የሆነች ኢትዮጵያ ብልሁ ሕዝቧ ለምን እንደሚራብ የተከበረ ጥናት መደረግ አለበት። ዋና ዋናዎቹን ምክንያቶች ፕሮፌሰር ስዩም ገላየ ደርድሯቸዋል። አንዱ፥ የመሬት ይዞታ መበላሸት ነው ይለናል። “የመሬት ላራሹ” ጩኸት ውጤቱ “መሬት ለነጋሹ” ሆኗል፤ ለገበሬው የታሰበውን መሬት ወያኔ ወሰደው። የዱሮ ንጉሣዊ ገዢዎቿ ቤተ ሰቦች ስለነበሩ በቊጥራቸው ማነስ ምክንያት እነሱን በማር ግብር ለማጥገብና በሰላም ለመኖር ቀላል ነበረ። የዛሬዎቹ ገዢዎች ብሔረ ሰቦች ስለሆኑ እነሱን ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ማጥገብ መራቆትን አስከትሏል። ሌላው፥ አገሪቱ በክልል መከፋፈል ነው። ማንም ሰው በገዛ ሀገሩ ከመሰለው ክፍለ ሀገር ሄዶ በሰፊው ማረስ አይችልም። ዛሬ ኢትዮጵያ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ሙሉ በሙሉ አገሩ አይደለችም። ኢትዮጵያ ለልጆቿ እናትነቷ በሙሉ ሰውነቷ እንዳይሆን ተከልክላለች።

Thursday, February 27, 2014

በማተብዋ ልዳኝ – ወድቃ የተነሳችው (ከስንሻው ተገኘ)


February 27, 2014
ከስንሻው ተገኘ
ወደ ትዝታ ዓለም ወደ ትዝታ ጊዜ በትዝታ ሰረገላ ልወስዳችሁ ነው። እኔ እንኳ በአጻጻፌ አበባዊ ቋንቋ አልወድድም። ለማንኛውም ግን አብረን እንድንነጉድ እጋብዛችኋለሁ። ወደ እንግሊዝ አገር! 1953 እ.አ.አ ወደ አንድ የለንደን ስብሰባ አዳራሽ እንገባለን። እንግዶች የነፃነት ታጋዮች ወደ አዳራሹ ከመግባታቸው በፊት የዌስት ኢንዲስ ተወላጅና የዓለም አቀፍ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ንቅናቄ መሪ የሆነው ጆርጅ ፓድሞን በአዳራሹ ውስጥ ፕሪዚደሙን ለብቻ ይዞታል። የእኔንና የእርስዎን ቡጢ (ጭብጥ) የሚያህል ወፍራሙን ትምባሆ (ቶስካኖ) ጐርሶአል። ጐርናና ድምፁ ሰውንም አዳራሹንም የሚቆጣጠር ዓይነት ነው። ከአፉ የሚወጣው ጢስ በአካባቢው አንዳች ዓይነት ጉም ሠርቶአል። በመካከሉ የሚያሰማው ባለ ግርማ የሆነው ሳሉ ለሰውየው ተጨማሪ ክብር አሸክሞታል።
The Green, Yellow and Red Ethiopian National Fla
“ክቡራትና ክቡራን! አዳራሹ ተከፍቶ ንግግር የሚያደርጉት የአፍሪካ ነፃነት ንቅናቄ መሪዎች ወደ ውስጥ ይዝለቁ!” ጆርጅ ፓድሞን ትእዛዝ ሰጠ። አዳራሹ ደግሞ ከግድግዳ እስከ ግድግዳ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አሸብርቆአል። በአራቱም ማዕዘናት ቄንጠኛ በሆኑ ረዣዥም ሰንደቆች ላይ ወርቃማና ቀለማማ በሆነ መደብ ላይ በጉልህ የሚታዩ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዎች አሉ። ትርኢቱ እንባ ካልጋበዘ ስሕተቱ የኔ ነው። ደካማ ጋዜጠኛ ሰነፍ ጸሐፊ…
አዳራሹ ተከፈተ። የማኦማኦ ንቅናቄ መሪ ወጣት የማይመስሉት ጆሞ ኬንያታ ብቅ አሉ። በደረታቸው ላይ የቀዳማዊ ኅይለ ሥላሴ ምስል ያለበት ፒን አድርገዋል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ እንደ ሻሽ አድርገው በራሳቸው ላይ ጠምጥመውታል። ቀጥል። የጐልድኮስቱ (በኋላ ጋና) የነፃነት ግንባር መሪ ካዋሚ እንኩሩማህ- ፈርጠም ያለ…ደልደል ያለ..ተክለ ሰውነታቸው ጉልህ የሆነ አርበኛ። ሰንደቅ ዓላማውን በሙሉ ለብሰውታል። የጃንሆይን ምስል ደግሞ በግራ ኮታቸው ክሳድ ላይ ሰክተውታል። ሑፍዌ ቩዋኘ (ኮትዲቮር) ሔስቲንግስ ባንዳ (ማላዊ) ወዘተ ተራ በተራ መጡ። ከመካከላቸው ጐፈር በራሳቸው ላይ ያደረጉ….በእጆቻቸው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልቡ የጃማይካ፣ የደቡባዊ አፍሪካ ታጋዮች ነበሩ። በብዙ ቁጥር። ሁሉም በመንፈስ ኢትዮጵያዊ ነበር። ያ ዘመን ደግሞ በትውልዱ ጃማይካዊ የነበረው ማርከስ ጋርቪ (Black nationalism and Pan-Africanism)ን እንዲሁም የራስ ተፈሪያኒዝምን ፍልስፍና የሚያስፋፋበት ነበር። የሁሉም አገር – ነፃነትዋን ለሺህ ዓመታት አስከብራ የኖረችው ኢትዮጵያ ናት።

“ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው”


ዑጋንዳ የጸረ ግብረሰዶማውያን ሕግ አጸደቀች!
musevini


የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡
ለበርካታ ዓመታት አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ ትላንት ዑጋንዳ አጽድቃለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም እና ሰዶማዊነት የመብት ጉዳይ እንደሆነ ከሚከራከሩ ተቋማት የደረሰባትን ውትወታ ወደ ጎን በማለት ዑጋንዳ በሕግ ማጽደቋ የበርካታ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን የሰጡበት ርዕስ ሆኗል፡፡ የሕጉን መጽደቅ አስመልክቶ ጥቂት ዑጋንዳውያን ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን በርካታዎች ደግሞ ድጋፋቸውን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡
uganda 1ሕጉን በፊርማቸው ያጸደቁት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ሲኤንኤን ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ግብረሰዶማውያን “አጸያፊ ሰዎች ናቸው፤ ምን ዓይነት ድርጊት ይፈጽሙ እንደሆነ አላውቅም ነበር፤ በቅርቡ የሰማሁት ግን በጣም አስደንጋጭ ነው፤ ጸያፍ ነው” ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሲቀጥሉም ሰዶማውያን ሲወለዱ ጀምሮ እንደዚሁ ናቸው ስለተባለ ሁኔታውን እውነት አድርገው በመውሰድ ቸል ሊሉት እንደነበር ሆኖም ግን እስካሁን ምንም ሳይንሳዊ ማስረጃ እንዳልቀረበበት ተናግረዋል፡፡
ሙሴቪኒ ሕጉን እንዲያጸድቁ ያደረጋቸውን አንዱን ምክንያት ሲጠቅሱም፤ ግብረሰዶማዊነት ከጄኔቲክስ ጋር በተያያዘ ከውልደት ጀምሮ የሚመጣ የተፈጥሮ ጉዳይ ነው በማለት ይገምቱ እንደነበር ሆኖም የአገራቸው ሳይንቲስቶች ይህንን መከራከሪያ ውድቅ ማድረጋቸውን ጨምረው ገልጸዋል፡፡
ሕጉ በፕሬዚዳንቱ ፊርማ ከጸደቀ በኋላ ወዲያውኑ በሥራ ላይ የዋለ ሲሆን ግብረሰዶማዊ ወሲብ ሲፈጽም የተገኘ ማንኛውም ሰው እስከ ዕድሜ ይፍታህ በሚደርስ እስራት እንደሚቀጣ ይደነግጋል፡፡ በወንጀሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ በ14ዓመት እስር ይቀጣል፡፡ በተደጋጋሚ ወንጀሉን ሲፈጽሙ የተገኙ፣ ዕድሜያቸው ካልደረሱ ጋር እንዲሁም ከአካለ ስንኩል ወይም ከኤችአይቪ ተጠቂ ጋር ወንጀሉን የፈጸሙ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ሕጉ ያዛል፡፡

ሀይለመድህን አበራ፦ የታፈነ ብሶተኛ ወይንስ የሚያደርገውን የማያውቅ የአእምሮ በሽተኛ?


February 27, 2014
አሰፋ (ከዳላስ)

መንግስትና የመንግስት ደጋፊዎች ነን ባዮች ማምታታቱን ትተው አንዱን መምረጥ አለባቸው

የሰሞኑ ትኩስ ዜና በሆነው የረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ የሚያበረውን አውሮፕላን ጠልፎ ስዊዘርላንድ ማሳረፉን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩ ነው:: በተለይ የኢትዮጵያው አገዛዝ እና እሱን አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ለመደገፍ የሚፈልጉ ሰዎች የሚስጡዋቸው መላምቶች የሚያስገርሙና እርስ በርሳቸው የሚጋጩ ናቸው:: ከነዚህ አስተያየቶች መካከል ሁለቱን ልጥቀስ:: በአንድ  በኩል ሀይለመድህን የአእምሮ ችግር አለበት ሲሉ በሌላ በኩል ደግሞ የሀገሪቱንም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስም ያጎደፈ በማለት ለመውቀስ ይዳዳቸዋል::
Ethiopian Airlines pilot Hailemeden Abera Tegegn
እንግዲህ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ እነዚህ ሁለቱ ግምቶችና ወቀሳዎች በአንድ ግዜ እና በአንድ ላይ እውነት ሊሆኑ አይችሉም:: አንዱ እወነት ከሆነ ሌላው ሀሰት ይሆናል:: ይህም ማለት ሀይለመድህን የአእምሮ በሽተኛ ከሆነ የኢትዮጵያንም ሆነ የአየር መንገዱን መልካም ገፅታ በማቆሸሽ ሊወቀስ አይችልም:: ምክንያቱም አንድ ሰው የአእምሮ ህመም አለበት ከተባለ በአእምሮ ህመም ውስጥ ሆኖ ለሚፈፅመው ድርጊት ሀላፊነት ሊወስድ አይጠበቅም:: አመዛዝኖና አስቦ ያደረገው ስላልሆነ:: ድርጊቱ በሰውየው እንደተፈፀመ ተደርጎ አይታሰብም:: ምክንያቱም ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ሀይል ተፅእኖ ስር ሆኖ ያደረገው የተከናወነ በመሆኑ:: በዚህም የተነሳ መልካም ነገር ቢሰራም ሊመሰገንና ሊሸለም እንደማይችል ሁሉ ክፉ ነገር ቢያደርግም ሊወቀስ እና ሊፈረድበት አይገባም:: ይህ ካልሆነ ግን የአእምሮ በሽተኛ የሚለውን ማንሳቱ ብዙም ትርጉም ሊኖረው አይችልም:: ስለዚህ መንግስትና የመንግስት ደጋፊዎች ነን ባዮች ማምታታቱን ትተው አንዱን መምረጥ አለባቸው::
ከላይ እንደገለፅኩት እውነት ሀይለመድህን የአእምሮ ችግር ወይንም የመንፈስ ጭንቀት ነበረበት ከተባለ ሊታዘንለት ይገባል እንጂ ሊወቀስ አይችልም:: ምናልባት ሊወቀስና ሊጠየቅ የሚገባው የአእምሮ ችግር ውስጥ ያለን ሰው አውሮፕላን ማብረርን የመሰለ ከፍተኛ የመንፈስ መረጋጋትን የሚጠይቅ ከባድ ስራ ውስጥ እንዲሰማራ ያደረገው ክፍል ይመስለኛል:: ለነገሩ ሀይለመድህን የሰራው ስራ በአእምሮ ጭንቀት ውስጥ ያለ ሰው ያደርገዋል ብሎ ማሰብ ፍፁም ይከብዳል:: አውሮፕላንን ያህል ነገር ከ200 በላይ ተሳፋሪ ጭኖ ያውም በሁለት የጦር ጄት አውሮፕላኖች እንደተከበበ አውቆ በተረጋጋ ሁኔታ በሰላም የሚፈልገው ቦታ ማሳረፍ መቻል አንድ የአእምሮ ችግር ካለበት ሰው የሚጠበቅ ድርጊት አይመስለኝም:: ይልቁንስ የሰከነ አስተሳሰብ ያለው እንዲሁም የሚያደርገውን ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው የፈፀመው ተግባር እንጂ የአእምሮ መረበሽ ውስጥ ያለ ሰው ድርጊት ያለመሆኑን አእምሮ ያለው የሚረዳው ነው::

Monday, February 24, 2014

Cloaking corruption in international respectability and credibility


February 24, 2014
The regime in Ethiopia is making a desperate second run to bring international respectability to its corrupt mining sector by re-applying for admission as an Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) candidate.  According to Anthony Richter, Chairman of the Board of the Revenue Watch Institute and a board member of the Extractive Industries Transparency Initiative (EITI), Ethiopia’s 2010 application was rejected because the  EITI
board concluded that Ethiopia’s ‘Proclamation on Charities and Society’ would prevent civil society groups from being sufficiently independent and meaningfully participate in the process.  The board decided, in effect, not to admit Ethiopia ‘until the Proclamation on Charities and Society is no longer in place.’ This is the only such instance in the history of EITI where a country has failed to be admitted and the grounds for this action was clearly rights-based. (Italics added.)
EITI is an international organization consisting of a “coalition of governments, companies, civil society, investors and international organisations” which “through robust yet flexible methodology company payments and government revenues from oil, gas and mining are published, and discrepancies are reduced.” Simply stated, EITI aims to promote accountability and transparency by requiring corporations and governments in  member countries to come clean on revenues generated in their extractive industries. EITI is widely recognized for its “standards that promotes revenue transparency at the local level.”

በአገሩ ሁለተኛ ደረጃ ዜጋ ሆኖ ባለሙያው እንዲበሳጭና እንዲማረር እያድረጉ የኢትዮጵያን አየር መንገድ መንከባከብና ማሳደግ ይቻላልን?


February 23, 2014
በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory
በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ ስለተንሰራፋው መጥፎ የማኒጅመንትና ብሄረስብ ላይ የተመሠረተ አስተዳደር ስለመኖሩ ብዙ ይነገራል። ታህሳስ 21፣ 1945 ተመሥርቶ: ረዥም ታሪክና ገና ከሥረ መሠረቱ በጥሩ የአስተዳደር ፍልስፍና ላይ የተመሠረተ በመሆኑ፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የነበረው የተመቻቸ ሁኔታ ለጥንካሬው ዋነኛ ምክንያት ሆኖታል።
የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ላይ አየር መንገዱ ሲቋቋም፡ ኢትዮጵያ በስሜንና በምሥራቅ የግዛት ክልሏ ራሱ እንኳ ገና አልተጠናቀቀም ነበር – የኤርትራ ሁኒታ አለየለትም። የዛሬይቱ ኦጋዴንም ተጠቃልላ ከእንግሊዝ ጋር በተደረገ በሕግ፡ በትሪቲ: ደንብና ድፕሎማቲክ ስምምነት ሙሉ የኢትዮጵያ አካል ለመሆን ገና ሁለት ዓመት ይቀረው ነበር።
ይህ የሚያሳየው አየር መንገዱና ኢትዮጵያ አብረው ያደጉና፡ ኢትዮጵያም ቀደም ሲል ለድህነንቷና ለግዛት አንድነቷ ታማኝነት በነበራቸው ሁለት መንግሥታት ሥር ለአየር መንገዱ የወደፊት ሕልውና እንደራሳቸው አካል ልዩ ትኩረት የሰጡት ኢንተርፕራይዝ ነበር። ባለፉት ሁለት አሥርተ ዓመታት ግን የሕወሃት የዘር ፖለቲካ አየር መንገዱንም እየተፈታተነው በመሆኑ፡ ውስጡ ያሉት ዜጎችም ሆኑ፡ ሌሎች ኢትዮጵያውንም የሚሰጉለት ድርጅት እየሆነ ነው።
ይህ ማለት ግን በእነዚህ ሁለት አሥርተ ዓመታት አየር መንገዱ አልተስፋፋም ማለት አይደለም – ብዙ ዕዳ ቢኖርበትም። ብዙ አውሮፕላኖች ተገዝተዋል፡ ብዙ የበረራ መስመሮች ተክፍተዋል። ነገር ግን የትኛውም ትክክለአኛ የማኔጅመንት ምሁር ሊያስረዳ እንደሚችለው፡ የአንድ ኢንተርፕራይዝ ጤንነትና አስተማማኝነት የሚለካው በዚህ ብቻ ቢሆንማ፡ ነገሮት ሁሉ ቀላል በሆኑ ነበር በዚህ በፉክክር በተወጠረ ኢንዱችትሪ ውስጥ።

Saturday, February 22, 2014

የሸፍጥ ክርክር የሃሰት ክምር የታሪክን እውነታ አይቀይርም! (ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ)


February 22, 2014
ከኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ
የካቲት 15 ቀን 2006 ዓ/ም ( February 22, 2014 )

I. መግቢያ:
የካቲት 3 ቀን 2006 ዓ/ም የወያኔ/ኢሕአዴግ ሊቀ-መንበርና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአገር-ውስጥ ጋዘጤኞች በሰጡት መግለጫ ላይ የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይን በተመለከተ ለቀረበላቸው ጥያቄ በድፍረት የሰጡት ምላሽ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴን ብቻ አይደለም መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ በእጅጉ ያሳዘነና ያሳፈረ ሆኖ አግኝተነዋል። በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እግር የተተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የተረከቡት የመንግሥት ሥልጣንን ብቻ ሣይሆን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከበሬታ-አልባነትንም በሚመስል መልክ ነው ይህንን በጣም የተምታታ፤ በተቃርኖዎች የተሞላና በእጅጉ ኃላፊነት-የጎደለው ጋዜጣዊ-መግለጫ የሰጡት።
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ባደረገው ያላሰለሰ ክትትል የወያኔ/ኢሕአዴግ መንግሥት ከሱዳን መንግሥት ጋር የሕዝብን መሠረታዊ-ሉዓላዊነት በሚዳፈርና ዘለቄታዊ ጥቅሙን ለባዕድ አሣልፎ በሚሰጥ ሁኔታ እየሸረበ ያለውን ደባና እየፈጸመ ያለውን አሣፋሪ ድርጊት በተገቢ ጥናትና በጠራ-መረጃ ላይ ተመሥርቶ በተከታታይ ባወጣቸው መግለጫዎች እንዲሁም በልዩ-ልዩ መገናኛ-ብዙኃን አማካይነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ለወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎችና ልዩ-ልዩ ተቋማት፤ ለሱዳን መንግሥትና ለዓለም-አቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር ሲያሳውቅ መቆየቱ ይታወቃል። የወያኔ/ኢሕአዴግ መሪዎች ግን አሁንም በዚህ የአገር ድንበርን በሚያክል ከባድ ጉዳይ ላይ ከዋናው ባለ-ጉዳይ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጀርባ የጀመሩትን እኩይ ተግባር እየገፉበት አንደሆነ ከራሣችው አንደበት እየሰማን ነው።
II. የመግለጫው ዓላማ፤
የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ በሚከተሉት ምክንያቶች ከላይ የተጠቀሰውን የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር በተመለከተ ይህንን መግለጫ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል።
ሀ). ከማንኛውም አገርና መንግሥት መሪ በተለይም የውጭ ግንኙንትን በተመለከተ የሚሰነዘር አስተያየትም ሆነ የሚሰጥ መግለጫ የአገር አቋም ተደርጎ የሚወሰድና በዋቢነትም የመጠቀስ መዘዝን ያዘለ በመሆኑ በዝምታ ሊታለፍም ሆነ ‘አጉል-መዘላበድ’ ተደርጎ ችላ ሊባል የሚችል ጉዳይ ባለመሆኑ፤