Sunday, March 16, 2014

Incarcerated Ethiopian journalist, Reeyot Alemu, spends 1000th day in prison


March 16, 2014
In a month when we are celebrating women, today, Sunday March 16th is Ethiopian journalist Reeyot Alemu’s 1000th day of imprisonment for simply doing her job.Ethiopian journalist Reeyot Alemu’s 1000th day of imprisonment
A columnist for several Amharic-language newspapers, Reeyot Alemu was one of the first journalists arrested in a 2011 government crackdown on dissent as authorities in Addis Ababa, unnerved by the Arab Spring revolutions, rounded up prominent journalists, intellectuals and political opponents and linked them to a vague terrorism plot.
While in pre-trial detention, she reported being pressured to sign a false confession to implicate co-defendants in imaginary crimes against the state.
Her refusal to cooperate earned her a sentence of 14 years in prison based on her newspaper columns in which she criticized the government’s record on corruption, its attacks on democracy and the rule of law, and the effects of repression on the population.
Her sentence was reduced to five years on appeal but she is pursuing an international appeal at the African Human Rights Commission.
Ms. Reeyot’s indomitable integrity and courage in defiance of the injustice of her imprisonment, has earned her international accolades such as the UNESCO-Guillermo Cano World Press Freedom Prize, the International Women’s Media Foundation Courage in Journalism Award, and a finalist spot for the Sakharov Prize for Freedom of Thought.
She is among eight journalists imprisoned in Ethiopia, Africa’s second worst jailer of journalists after Eritrea.

“እኛና አብዮቱ” የሻምበል ፍቅረሥላሴ ወግ ደረስ ጸጸት አልባ ትዝታዎች


March 16, 2014
ከኤፍሬም የማነብርሐን
ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግ ደረስ በጣም አስደናቂም አስገራሚም የሆነ መጽሐፍ ለንባብ አብቅተዋል። የደርግ አባልና ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ለአምባ ገነኑ ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም እንደቀኝ እጅ ባገለገሉበት ዘመን የሆነውን ሁሉ እሳችው ካመኑበት አቋም በመንደርደር ተርከውታል።  በጣም ብዛት ያላቸው የውስጥ ሰው ብቻ ሊያውቃቸው የሚችላቸው መረጃዎችን (ፋክትስ) መጽሐፉ አካቷል።  ብዙ ሰው ወደ ጀርባ ገፍቶት የነበረውን የዚያን የደም ዘመን ትዝታዎች እንደ አዲስ ይቀሰቅሳል።  ደራሲው መረጃዎችን በመሰብሰብና በተቀናጀ መልክ ታሪኩን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በማቅረባቸው ሊደነቁ ይገባል። ታሪክም ላቀረቡት ጽሑፍ እንደባለውለታ ያያቸዋል የሚል ግምት አለኝ።  የዚያ አስከፊና በኢትዮጵያ ላይ የማይሽር ጠባሳ ጥሎ ያለፈው የደርግ ቡድን አባል በመሆን ከድርጅቱ የተቆራኙ ቢሆኑም፣ ጽሑፉን በማዘጋጀታቸው ለአገር፣ ለወገን በአመዛኙ ጠቃሚ አስተዋጽኦ ለማቅረባቸው መጽሐፉ ቋሚ ምስክራቸው ይሆናል።
Former Ethiopian official Fikreselasie Wegderes new book
መጽሐፉ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴን መንግስትና የገዢውን የፊውዳል ሥርዓት ለማንበርከክና ደርግ በሥልጣን ተፈናጦ ለመቀመጥ እንዲያስችለው እርምጃዎች በወሰደ ቁጥር ያጋጠሙትን ተቃውሞዎች፣ የብሔራዊ ዘመቻንና የሶማሌን ወራሪ ጦር ለመመከትና ወደመጣበት ለመመለስ የተደረገውን ርብርቦሽና በተለይ አኩሪ የሆነውን የታጠቅ ጦር ሠፈር ግንባታና አስተዋጽኦ፣ የገጠርና የከተማ ቤት አዋጆችን ለማውጣትና ለማሰፈጸም የተደረጉ ጥረቶችንና ቅዋሜዎችን፤ የፖለቲካ ቅራኔዎችን ለመግታት፣ ለመገደብ፣ ለማምከንና ብሎም የኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያምን አምባ ገነንነት ለማረጋገጥ የተደረጉ ፍልሚያዎችን በሰፊው ተንትኗል።

Blue Party’s executives and female members are being accused of freedom of expression!


March 14, 2014
BlueParty Ethiopia
Early in the morning many gathered at the compound of the court house. The appearance was expected to be held at 10:00AM yet only the men arrived. It took the police about an hour after to bring the girls. Most were worried. Then we heard they were being forced to change their shirts that they put on. But they refused to change. After some quarrel at the police station finally they arrived at the court house at 11:08AM.
Blue Party’s executives and female members are being accused
The court house was full of people, some even stood and it was quite humid. After the judge took his place the ones stood were much in number than those who sat. The attorney of the suspected and The Inspector how is handling the case stood by the sides; amid was Blue Party’s young members and leaders of high position.
The case was of course presented 5 days ago and ended with denying a bail for the young activists and members of the party because they were believed to terrorize and as well suspected of disturbance on Women’s Great Run which ended way peacefully.

Wednesday, March 12, 2014


March 11, 2014
ቹቸቤ
የሰማያዊ ፓርቲ ቢጫ ለባሽ ወጣት ሴቶች መታገታቸውን ሰምተን ነበር። አንጋፋው ክስ ደግሞ እናትና አባታቸውን ጮክ ብለው መጥራታቸው መሆኑ ሲነገረን የጥፋታቸው ልክ ታሰበን። የትግራይ ናፃ አውጪዎችና ለነርሱ ለመታዘዝ ፈቃዳቸውን ያሳዩ ገባሪዎች በሙሉ ለተልዕኮ ትምህርት የማይመቹትን እነ ባዮሎጂንና ኬሚስትሪን ዞር አላሉባትም። በርካቶቹ የራሳቸውን ስም ከረሱ የቆዩ ስለሆኑ ዘር በጅምላው እንጂ ቤተሰብ በነጠላው አይገባቸውም። እናም እነዚህ ወጣቶች የሚኒሊክና የጣይቱ ልጆች ነን ማለታቸው አሸበራቸው።
Arrested Semayawi party members and supporters
ትንሽ እወቀት ያለን እኛ ግን በመጀመርያ ሴቶች ወላጅም አዋላጅም መሆናቸውን እናውቃለንና የሚኒሊክና የጣይቱ ልጆች ነን ቢሉ አይደንቀንም። እንዲያውም “ጎሸ ሰው ጫካ በቀል አጉራ ዘለል ሲሆን ነው እንጂ የመጣበትን ሲያውቅ ጥሩ ነው።” ብለን ያደነቅን እናቅፋለን የወደድን ለጋብቻ እንጠይቃለን። ወጉ እንደዚህ ነዋ! በጋብቻ ተደራጅቶ የሚኒሊክና የጣይቱን ስም ማቆየት ስለምን ያስፈራል? ዘር መተካት ደግ ነው እንላለን። እንዴ ፌዴራሎች ጠለፋ ይሆን እንዴ የፈፀሙት?
ቢሆንም ልካቸውን ያውቁታልና በሚኒሊክና ጣይቱ በሚሸበሩትም አንፈርድም። ግንቦት ሃያ የተወለዱት ራሳቸውን የፋብሪካ ውጤት አድርገው ስለሚቆጥሩ ተጋዳላይ ድርጅት እንጂ እናትና አባት እንዴት ሊኖረው ይችላል ብለው የመቆጣት መብታቸውንና የማስፈራራት አቅማቸውን ተጠቅመዋል። እናም ድንጋይ ሰባሪ ቅሎቹ ወይም ባለጊዜዎቹ እነዚህን የሚያማምሩ የሚኒሊክና የጣይቱ ልጆችን ተመሳስለው የገቡ ጠጉረ ልውጦች ብለዋቸዋል።

የአባ መላ (ብርሃኑ ዳምጤ) መገለባበጥና ኢሳት


March 11, 2014
እንደልቡ/ዳግም (ከቫንኮቨር፣ ካናዳ)
አባ መላ ማን ነው?
በቅጽል ስሙ “አባ መላ” በእውነተኛ ስሙ ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ ተብሎ ይጠራል፣ በ60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ አዛውንት ነው (ምንም እንኳ ስራው እንደ እድሜው ባይሆንም)። ፓልቶክ የሚባለውን የማህበራዊ መገናኛ መድረክ በመጠቀም በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ዲስኩር በማሰማት ይታወቃል። በወጣትነቱ ኢህአፓ ውስጥ ነበር የሚባለው ብርሃኑ ዳምጤ ወዲያውም የኢህአፓን መዳከም አይቶ ወደ ደርግ ቡድን መቀላቀሉን የሚያውቁት ይናገራሉ። በወቅቱ አብረውት በኢህአፓ ውስጥ ይሳተፉ የነበሩ ወጣቶችን ለደርግ በእጅ መንሻ መልክ አሳልፎ ሳይሰጥ እንዳልቀረ በደርግ ካድሬነት ቆይታው የሚያውቁት ይጠረጥራሉ አንዳንዶች ደግሞ አፋቸውን ሞልተው ይናገሩታል።
Aba Mela low rank Ethiopian government cadre
ብርሃኑ ዳምጤ ከደርግ መውደቅ በኋላ በስደቱ ዓለም (ዳያስፖራ) ፖለቲካ መድረክ ብቅ ያለው በምርጫ 97 ወቅት የዝነኛውን ቅንጅት ማልያ ለብሶ ነበር። ይሁንና በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት/ወያኔ መንግስት ምርጫውን አጭበርብሮ፣ የምርጫውን መጭበርበር የተቃወሙትን በገፍ በአደባባይ በጥይት ደብድቦ፣ ህዝቡ የመረጣቸውን የቅንጅት አመራሮች፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችን ጨመሮ ከ50 ሺህ በላይ ባብዛኛው ወጣቶችን አስሮና በየጦር ካምፖቹ አጉሮ በአምባገነንነቱ ለመቀጠል ሲወስን ብርሃኑ ዳምጤም ባፋጣኝ የቅንጅትን ማልያ አውልቆ የህወሃት/ኢህአዴግን ማልያ ለብሶ ቁጭ አለ።
ሰሞኑን ደግሞ ብርሃኑ ዳምጤ አስደናቂ መገለባበጥን ፈጽሞ የህዝብን አይን አስበልጥጧል። እነዚህ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) ሰሞኑን የሚፈጽማቸው መገለባበጦች በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ ከነበሩት የመገለባበጥ ትሪኢቶቹ ለየት የሚያደርጋቸው ነገር ቢኖር አሁን መገለባበጡን የሚፈጽመው በቀጥታ ስርጭት ወቅት (በፓልቶክ) መሆኑና ጉዳዮን በመሪ ዜና መልክ የሚዘግብለት የቴሌቪዥን ጣብያ “ኢሳትን” ማግኘቱ ነው።
ብርሃኑ ዳምጤ ከጥቂት ወራቶች በፊት ነበር የተሰለፈበት የህወሃት/ኢህአዴግ ጎራ በተለይም ከወያኔው ቁንጮ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ እየተዳከመ መምጣትን አይቶና ገምቶ ወያኔዎችን “አፍንጫችሁን ላሱ፣ እኔ ከአሁን ብኋላ የድሮው አባ መላ አይደለሁም፣ እንዲያውም ጉዳችሁን አዝረጠርጣለሁ…” በማለት ፉከራ ቢጤ አሰምቶ የዲሞክራሲና የነጻነት ታጋዮችን ጎራ መቀላቀሉን ያበሰረው።

Monday, March 10, 2014

የሴት ነገር ሰማያዊ በቢጫ (ከቹቹቤ)



Ethiopian women protested in Addis Ababa
በተለምዶ የሴት ነገር ስንል የማሳነስ የማቀጨጭ ነው። የሴት ነገር ግን ሁሌም ቢሆን ከዚህ በላይ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን። የሴትን ነገር የሚያሳንሱ ቢኖሩ ጉልበት አምላኪዎች ብቻ ናቸው። አርግዛ አምጣና ወልዳ የምታሳድግን ሴት እንደ ቅርንጫፍ ከጎድን አጥንት ተሰራች የሚለው አሳናሽ አገላለጽም የሃይማኖት ድጋፍ ይዞ ስለተነሳ ሴቶች ራሳቸው ያነሱ ሆነው እስከሚሰማቸው ድረስ ተጽዕኖ አሳዳሪ መሆኑ እውነት ነው። ዘፍጥረት ወንዴና ሴቴ ሆነው የተፈጠሩትን ሌሎች ፍጡራን (እንስሳውን እጽዋቱን) ሁሉ እግዜር እንዴት እንደፈጠራቸው መናገሩን አላውቅም።  የኔዋ እናት ግን በምንም መልኩ ከኔው አባት አንሳ የጎድን ፍልቃቂው ልትሆን አይቻላትም። እንዴት ተደርጎ! እኔም በማህጸን ውስጥ ሞተር ሲገጠምልኝ፣ እግርና እጅ ሲሰራልኝ አፍንጫ ጆሮና አይኔ ዲዛይን ሲደረግ ስለቆየሁ እርሷ የኔ ፈጣሪ ናት ብዬ ነው እምዬ ስላት ደስ የምሰኘው። እርግጥ ነው የተወሰነ ጥሬ ሃብት ከአባቴ ወስዳለች። በዚያው አይን የኔ የምትሆነው ሴቲቱ ከጎድኔ አንዱ ተቀንሶ እንደተሰራች መቀበል ያዳግተኛል። በእንስሳቱ አለም የሴቶች ሚና እጅግ በጣም ጉልህ መሆኑን ለተመለከተ የሰው ፍጡር ሲሆኑ ሊያሳንስበት የሚችልበት ምንም ምክንያት የለውም። በተለይ በማህበራዊ እንስሳትም ሆነ ነብሳት ውስጥ ሴቲቱ አልፋና ኦሜጋ ናት። ቢሆንም…..ቢሆንም አውቄ በድፍረት ሳላውቅ በስህተት ላልኩት ንስሃ ልግባና ሰማያዊ በቢጫ እንዴት ደስ እንዳሰኘኝ ልናገር።

Sunday, March 2, 2014

ዕርቅና ሰላም፤ የሕይወት ቅመም (ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ)


March 2, 2014
ከፕ/ር ጌታቸው ኃይሌ
አንድ ጥናት ሳነብ፥ ምናልባት እናንተም አንብባችሁት ይሆናል፥ የተፈጥሮ ሀብት ባላት ሀገር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ከተራቡ፥  የማሰብ ችሎታቸው ዝቅተኛ ቢሆን ነው ሲል አገኘሁት። “ጥልቀት የሌለው ረጋ-ሠራሽ ጥናት ነው” ብዬ ጣልኩት። የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ባለጠጋ መሆኗን እርግጥ ባለሞያዎች የመሰከሩት ነው። ማዳበሪያ የማያስፈልገው መሬት ታርሶ አያልቅም። የወንዞቿ ውሀ ለጎረቤት አገሮች ሳይቀር ይተርፋል። ይኸንን እውነታ በቀጥታ ከተመራማሪዎቹ  አፍ ለመስማት የፈለገ ፕሮፌሰር ስዩም ገላየን ማዳመጥ ይችላል።
Prof Getachew Haile Ethiopia
እንዲህ ከሆነ፥ ትኩረቱ በኢትዮጵያውያን የማሰብ ችሎታ ላይ ሊሆን ነው። እውነት የኢትዮጵያ ሕዝብ ተመጽዋች ሆኖ የቀረው የማሰብ ችሎታው ዝቅተኛ ሆኖ ነው? አይመስለኝም።  ሰውየው ጥናቱን ማስተካከል አለበት። አለዚያ፥ ከዚያ ቀጥሎ፥ “አንድ ሰው እሱቁ ውስጥ ከመስተዋቱ በስተኋላ ድፎ ዳቦ እያየ ከተራበ የአስተሳሰብ ችሎታው ዝቅተኛ ቢሆን ነው” ሊለን ነው። ምንም ከፍተኛ የማሰብ ችሎታ ቢኖረው፥ ዳቦውን እንደማያገኘው ለማንም ግልጽ ነው።
እርግጥ ነው፥ በአስተሳሰብ ደከም የሚል ሰው ሊጎዳ ይችላል። ሌላው ቢቀር፥ የብልሁ ጓደኛውን ያህል አይደላውም።  ግን በከፍተኛ ደረጃ የማሰብ ችሎታ ያለው ሰውም ሊቸገር ይችላል።  ስንቶች ናቸው ኢትዮጵያ ውስጥ በችግር የሚኖሩ፥ መውጫ ቢያገኙ ግን ለሌላው ሳይቀር የሚተርፉ? በአፍሪካ፥ በአውሮፓ፥ በአሜሪካ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ በማስተማርና በምርምር ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያን ቊጥር ቀላል አይደለም። በንግዱ ዓለምም ቢሆን፥ “የሺ ብር ጌቶችን” ጓዳ ይቊጠራቸው።
የለም፥ የተፈጥሮ ሀብት ባለጠጋ የሆነች ኢትዮጵያ ብልሁ ሕዝቧ ለምን እንደሚራብ የተከበረ ጥናት መደረግ አለበት። ዋና ዋናዎቹን ምክንያቶች ፕሮፌሰር ስዩም ገላየ ደርድሯቸዋል። አንዱ፥ የመሬት ይዞታ መበላሸት ነው ይለናል። “የመሬት ላራሹ” ጩኸት ውጤቱ “መሬት ለነጋሹ” ሆኗል፤ ለገበሬው የታሰበውን መሬት ወያኔ ወሰደው። የዱሮ ንጉሣዊ ገዢዎቿ ቤተ ሰቦች ስለነበሩ በቊጥራቸው ማነስ ምክንያት እነሱን በማር ግብር ለማጥገብና በሰላም ለመኖር ቀላል ነበረ። የዛሬዎቹ ገዢዎች ብሔረ ሰቦች ስለሆኑ እነሱን ሁሉ በሚሊዮን ዶላር ማጥገብ መራቆትን አስከትሏል። ሌላው፥ አገሪቱ በክልል መከፋፈል ነው። ማንም ሰው በገዛ ሀገሩ ከመሰለው ክፍለ ሀገር ሄዶ በሰፊው ማረስ አይችልም። ዛሬ ኢትዮጵያ ለአንድ ኢትዮጵያዊ ሙሉ በሙሉ አገሩ አይደለችም። ኢትዮጵያ ለልጆቿ እናትነቷ በሙሉ ሰውነቷ እንዳይሆን ተከልክላለች።